11.5 C
Addis Ababa
September 21, 2021
Local News

የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለሁለተኛ ጊዜ ሀገር አቀፍ የጥጥ ልማት የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ፡፡

የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የንቅናቄ መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን አሁን ደግሞ በጋምቤላ ከተማ ባሮ ጋምቤላ ሆቴል ግንቦት 25/2013 ዓ.ም የጥጥ ምርትን አስመልክቶ በክልሉ የሚገኙ ጥጥ አልሚ ባለሀብቶችን ፣ የሚመለከታቸው አመራሮችንና የዘርፉ ባለሙያዎችን አወያይቷል ፡፡ በውይይቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ዋነኛው ጥጥ እንደመሆኑ መጠን ለጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በቀጣይ ዓመት የግብአት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት አስቀድሞ መዘጋጀትና ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ የዘርፉ ባለድርሻዎች ሀላፊነት መሆኑ በስፋት ተብራርቷል፡፡
 
የጋምቤላ ክልል ኢትዮጵያ ካሏት ለጥጥ ልማት ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል አንዱ በመሆኑ የክልሉን አምራቾች ማነቃነቅና ስራቸውን አዘምነው ተገቢውን ምርት ማምረት እንዲችሉ ማድረግ የንቅናቄ መድረኩ ዋና ዓላማ እንደሆነ በመርሀ ግብሩ ላይ በተደረገው ገለፃ ማወቅ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም አብዛኞቹ ያደጉ ሀገራት አራተኛውን የኢንዱስትሪ የዕድገት ደረጃ ሊደርሱ የቻሉት ከጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ተነስተው ነው፡፡ለዚህ ኢንዱስትሪ ደግሞ ዋነኛ ግብአት ጥጥ ነው፡፡ ስለሆነም በ2012/13 የምርት ዘመን በአፋር ክልል በጎርፍ ምክንያት የደረሰው አደጋና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተከሰተው የፀጥታ መቃወስ ሳቢያ የተፈጠረውን የግብአት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ሀላፊነት ስላለብን በዘር ወቅት አምራቾችና የዘርፉ አመራሮች በቅንጅትና በትጋት መስራት አለብን ሲሉ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሰለ መኩሪያ አስገንዝበዋል፡፡
Source: https://www.facebook.com/ethiopian.textile.3

Related posts

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Areda Batu

የሞጆ የጋራ ፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

Areda Batu

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወተር ዊትነስ ኢንተርናሽናል ከተባለ የልማት ድርጅት ጋር የ21 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ ::

Areda Batu

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy
Show Buttons
Hide Buttons