14.5 C
Addis Ababa
April 25, 2024
Local News

በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ያለውን የክህሎት ፍላጎት አስመልክቶ የተሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ አሻም አፍሪካ ሆቴል ከጥቅምት1/2014 እስከ ጥቅምት 5/2014 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሀገሪቱ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ያለውን የክህሎት ፍላጎት መለየት የሚያስችል የስልጠና መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡ስልጠናው በኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትና በዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ከዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት በመጣች ከውጭ ዜጋ ጋር የልምድ ልውውጥ ከመደረጉ በተጨማሪ በዋናነት ሀገር አቀፉና ዓለም አቀፉ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ያለበትሁኔታ፣ለዘርፉ ኢትዮጵያ ያላት የአስር ዓመት ዕቅድ፣የኢንዱስትሪዎች ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት፣የሙያ ደረጃ አሰጣጥና ሀገር አቀፍ ስትራቴጅዎችን የሚመለከቱ ገለጻዎች ከቀረቡ በኋላ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በውይይቱም ፋብሪካዎች ግልጽ የሆነ ራዕይ፣ዓላማና ተልዕኮ አስቀምጦ ከመስራት ባሻገር በስራቸው ላሉ ባለሙያዎች ከግባቸው አኳያ ተስማሚ የሆነ የስልጠና መርሀ ግብር ማመቻቸት እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ይህንንም በተሳካ ሁኔታ ማስኬድ ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የስልጠናና የስራ መመሪያዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡በመጨረሻም በውይይቱ የተካተቱ ዓበይት ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በተደረገው የስራ ክፍፍል መሰረት ሁሉም ባለድርሻ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ሲሉ በኢንስቲትዩቱ የሽመናና ሹራብ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እናውጋው ንጉሴ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Source: https://www.facebook.com/ethiopian.textile.3

 

Related posts

An agreement was signed to organize and make the information of national manufacturing industries accessible

Areda Batu

An Updated Approach to Addressing Foreign Exchange Supply Challenges in the Manufacturing Industry

Areda Batu

Bahir Dar University Opened an Exhibition for the University Community on June 5, 2023, Showing 60 years of Journey.

Areda Batu

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy
Show Buttons
Hide Buttons